Metemamen Microfinance S.C.

አስራ ሶስተኛ (13) አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

ለመተማመን ማይክሮ ፈይናንስ  አ.ማ

ባለአክሲዮኖች በሙሉ

በያሉበት

አስራ ሶስተኛ (13) አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ሰኞ ታህሳስ 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ፒያሳ ካቴድራል ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የኢትዮያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት (ECS) የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡

  1. አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
    • የአ.ማ. ስም፡-                             መተማመን ማይክሮ ፈይናንስ  አ.ማ.
    • የአ.ማ. ዓይነት፡-                        በአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ
    • የአ.ማ. የተፈረመ ዋና ገንዘብ፡-   በብር 838,736,000
    • የአ.ማ የተከፈለ ዋና ገንዘብ፡-      በብር 579,561,000
    • የምዝገባ ቁጥር፡                         KK/AA/3/0015811/2014
    • የሥራ ፍቃድ ቁጥር፡-                MFI/020/2002
    • የዋና መ/ቤት አድራሻ፡-            አ.አ. ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 995 ስልክ   +251 – 11- 3698246/86 ድረ ገፅ metemamen.com
  2. የ13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ አጀንዳዎች
    • የጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ ማፅደቅ
    • ተሻሽሎ በቀረበው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
    • ተፈርመው ባልተከፈሉ አክሲዮኖች አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን
    • የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ በንባብ ማሰማትና ማጽደቅ
  3. ማሳሰቢያ
    • ባለአክሲዮኖች በስብሰባው ላይ ለመገኘት ማንነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ፣ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
    • በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ በተሰጠ ውክልና ወይም በንግድ ሕጉ አንቀፅ 377 መሰረት ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን 3 /ሶስት/ ቀናት በፊት የማኅበሩ ዋና መ/ቤት ማንነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ፣ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በመቅረብ የውክልና መስጫ ቅፅ መሙላት ይችላሉ
    • አንድ ባአክሲዮን በአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም በስራ ላይ ያሉ የአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና ሠራተኞች ባለአክሲዮኖችን በመወከል በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት በጉባኤው ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
    • ባለአክሲዮኖች በስልክ ቁጥር 0113 69 82 46/86 በመደወል ተጨማሪ መረጃዎችን
      ማግኘት ይችላሉ፡፡

መተማመን ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.

            የዳይሬክተሮች ቦርድ

Scroll to Top